ወልደ ፡ አብ ፡ በወልደ ፡ አብ : ክፍል ፡ ሁለት
==================================
የጌታችን ፡ የባሕርይ ፡ ልጅነት ፡ እና
የቤተ ፡ አይሁድ ፡
ካሮች ፡ ውድቀት
======================================
በገዛ
፡ ሥልጣኔ ፡ ተነሣሁ ፡ ሲል ፡ ለወልድ ፡ ከአብ ፡ ከመንፈስ ፡ ቅዱስ ፡ የተለየ ፡ ሥልጣን ፡ አለውና ፡ በተለየ ፡ ሥልጣኔ
፡ ተነሣሁ ፡ ሲል ፡ ነውን? ፡ ቢሉ ፤ ከአብ ፡ ከመንፈስ ፡ ቅዱስ ፡ ጋር ፡ በሥልጣን ፡ ዕሪናውን ፡ ሲያጠይቅ ፡ እጅ ፡
የተነሣስ ፡ በ3ቱም ፡ ሥልጣን ፡ ነው ፡፡ “አማን ፡ በአማን ፡ ተንሥአ ፡ እሙታን ፡ በኃይለ ፡ አቡሁ ፡ ወመንፈስ ፡ ቅዱስ ፡ በሥልጣኑ ፡
ፈቲሆ ፡ ማዕሠሮ ፡ ለሞት()” ፡ እንዳለ ፡ ድርሳነ ፡ ማኅየዊ() ፡፡ በ3ቱም ፡
ሥልጣን ፡ እንደተነሣ ፡ ሊቃውንቱ ፡ በዝርዝር ፡ ተናረዋል ፡፡
በአብ
፡ ሥልጣን ፡ እንደተነሣ ፡ ቅዱስ ፡ ጳውሎስ ፡ “አብ ፡ አንሥኦ ፡ ለወልዱ ፡ እሙታን” ፡ ብሏል ፡፡ በገዛ ፡ ሥልጣኑ ፡ እንደተነሣ
፡ ቅዱስ ፡ ቄርሎስ ፡ “ወተንሣእኩ ፡ በሥልጣነ ፡ ባሕቲትየ” ፡ ብሏል ፡፡ በመንፈስ ፡ ቅዱስ ፡ ሥልጣን ፡ እንደተነሣ ፡ ባስልዮስ
፡ ዘቂሣርያ ፡ “ወተንሥአ ፡ በኃይለ ፡ መለኮቱ” ፡ ብሏል(ሃይ.አበው
፡ ምዕ ፡ 34 ፡ ክ
፡ 5 t ፡ 18) ፡፡
ኃይል ፡ የተባለ ፡ መንፈስ ፡ ቅዱስ ፡ እንደሆነ ፡ ለማጠየቅ ፡ ወንጌለ ፡ ሉቃስ(ምዕ ፡ 24 ፡ t ፡ 49) ፡
“ወናሁ ፡ እፌኑ ፡ ተስፋሁ ፡ ለአቡየ(እኔም ፡ ተስፋ ፡ መንፈስ ፡ ቅዱስን ፡ እልክላችኋለሁ) ፡ ወአንትሙሰ ፡ ንበሩ ፡ ሀገረ
፡ ኢየሩሳሌም ፡ እስከ ፡ ትለብሱ(እናንተ ፡ ግን ፡ ከሰማይ ፡ ሀይልን ፡ ማለት ፡ ሰማያዊ ፡ ሀብትን ፡ እስክትለብሱ ፡ በኢየሩሳሌም
፡ ኑሩ)” ፡ ብሏል ፡፡ይህስ ፡ ይሁን ፡ በሥልጣነ ፡ ባሕቲትየ ፡ ማለቱ ፡ በብቻየ ፡ ሲል ፡ አይደለምን? ፡ ቢሉ ፤ ይህስ
፡ ትንሣውን ፡ ሲያይ ፡ የተናረው ፡ ነው ፡፡ ማለትም ፡ አብና ፡ መንፈስ ፡ ቅዱስ ፡ እንደሱ ፡ ሰው ፡ አልሆኑም ፤ እሱ ፡
ግን ፡ ሰው ፡ የሆንኩ ፣ ከሙታን ፡ የተነሣሁ ፡ በተለየ ፡ አካሌ ፡ እኔ ፡ ብቻ ፡ ነኝ ፡ ሲል ፡ “ወተንሣእኩ ፡ በሥልጣነ
፡ ባሕቲትየ” ፡ አለ ፡ እንጅ ፡ ከአብና ፡ ከመንፈስ ፡ ቅዱስ ፡ የተለየ ፡ ሥልጣን ፡ አለኝ ፡ ሲል ፡ አይደለም ፡፡
ዳግመኛም
፡ የጸጋ ፡ ልጅ ፡ የግድ ፡ ይታመማል ፣ የግድ ፡ ይሞታል ፡ እንጅ
፡ በፈቃዱ ፡ አይታመምም ፣ በፈቃዱ ፡ አይሞትም ፤ እርሱ ፡ ግን ፡ የባሕርይ ፡ ልጅ ፡ ነውና ፡ በፈቃዱ ፡ ታመመ ፡ ሞተ ፤
“ሞተ ፡ በፈቃዱ ፡ ወተቀብረ ፡ በሥምረቱ” ፡ እንዳለ ፡ ዮሐንስ ፡ ነባቤ ፡ መለኮት ፡፡ ዳግመኛም ፡ የጸጋ ፡ ልጅ ፡ የራሱን
፡ ይታመማል ፡ ይመሞታል ፤ “እመሰ ፡ ኀደረ ፡ ቃል ፡ ላዕሌሁ ፡ ከመ ፡ ኵሎሙ ፡ ነቢያት ፡ ለምንትኑ ፡ ኢተብህለ ፡ በእንተ
፡ ግብሮሙ ፡ እምልደቶሙ ፡ እስከ ፡ ዕለተ ፡ ሞቶሙ ፡ ኮነ ፡ በእንቲአነ ፡ አላ ፡ በእንተ ፡ ርእሶሙ ፡ ባሕቲቶሙ(በነቢያት
፡ ሁሉ ፡ እንዲያድር ፤ ቃል ፡ ከአደረበት ፡ ከተወለዱ ፡ ጀምሮ ፡ እስከ ፡ ሞታቸው ፡ ድረስ ፡ የሠሩት ፡ ሥራ ፡ እኛን ፡
ለማዳን ፡ ተደረገ ፡ ለምን ፡ አልተባለም? ፡ ራሳቸውን ፡ ብቻ ፡ ለማዳን ፡ እንደሆነ ፡ ተነገረ ፡ እንጅ ፡፡
እመሰ
፡ ኀደረ ፡ ላዕሌሁ ፡ ቃል ፡ ከመ ፡ ኩሎሙ ፡ ነቢያት(በነቢያት ፡ ሁሉ ፡ እንዲያድር ፡ ቃል ፡ ከአደረበት) ፤ ለምንትኑ ፡
ተብህለ ፡ በእንተ ፡ ዝንቱ ፡ ባሕቲቱ ፡ ዘተወልደ ፡ እምእግዝእትነ ፡ ቅድስት ፡ ድንግል ፡ ማርያም ፡ ምዕረ ፡ ቦአ ፡ ውስተ
፡ ዓለም ፡ በደኃሪ ፡ መዋዕል(ከእግዝእትነ ፡ ማርያም ፡ ስተወለደ ፡ ስለእርሱ ፡ ብቻ ፡ 5500 ፡ ዘመን
፡ ሲፈጸም ፡ አንድ ፡ ጊዜ ፡ ሰው ፡ ሁኖ ፡ ተወለደ ፡ ተብሎ ፡ ለምን ፡ ተነገረ)” ፡ እንዳለ ፡ አትናቴዎስ(ሃይ.አበው ፡
ምዕ ፡ 31 ፡ t ፡ 31-32) ፡፡
ጌታ ፡ ግን ፡ የባሕርይ ፡ ልጅ ፡ የባሕርይ ፡ አምላክ ፡ ነውና ፡ ለሰው ፡ ብሎ ፡ ታመመ ፡ ሞተ ፤ “ሞተ ፡ ከመ ፡ ያሕይዎሙ ፡ ለምውታን” ፡ እንዳለ ፡ ዮሐንስ ፡ ነባቤ ፡ መለኮት ፡፡
ምነዋ
፡ የጸጋ ፡ ልጆች ፡ ጻድቃን ፣ ሰማዕታት ፡ መታመማቸው ፣ መሞታቸው ፡ በፈቃዳቸው ፡ አይደለምን?፡ እንደምን ፡ የግድ ፡ ይሆናል?
፡ ቢሉ ፡ ጌታ ፡ ሲአስተምር ፡ በወንጌለ ፡ ማቴዎስ(ምዕ ፡ 1 ፡ t ፡ 36)
፡
ላይ ፡ “ዘኢሐደገ ፡ አባሁ ፡ ወእሞ ፣ ቤቶ ፡ ወዉሉዶ ፡ ወዘኢፆረ ፡ መስቀለ ፡ ሞትየ ፡ ኢይክል ፡ ይፀመደኒ” ፡ ብሎ ፡
እንደገለጸው ፤ እናት ፡ አባቱን ፣ ቤት ፡ ንብረቱን ፡ ትቶ ፡ እኔን ፡ ያልተከተለ ፡ ከእኔ ፡ አንድነት ፡ የለውም ፡ መንግሥተ
፡ ሰማያትን ፡ እንኳንስ ፡ ሊገባባት ፡ አያያትም ፡ ብሎ ፡ አዋጅ ፡ ተናግሯል ፡፡ ጻድቃን ‹ ሰማዕታትም ፡ ይህ ፡ አዋጅ ፡
ግድ ፡ ብሏቸው ፡ ይታመማሉ ፡ ይሞታሉ ፡ እንጅ ፡ በፈቃዳቸው ፡ አይታመሙም ፡ አይሞቱም ፤ እሱ ፡ ግን ፡ ይጸድቅበታል ፡ እንዳይባል
፡ በባሕርዩ ፡ ጻድቅ ፤ ይብርበታል ፡ እንዳይባል ፡ የባሕርይ ፡ ክቡር ፡ ነውና ፡ ለሰው ፡ ሲል ፡ በፈቃዱ ፡ ታመመ ፡ ሞተ
፡: