ዕዝራ ሐዲስ Vs ዕዝራ ሱቱኤል ክፍል ሁለት

 


ከቅዱስ ቄርሎስ ድርሳን የተወሰደ /የብራና/

በክርስቶስ ክርስቲያን በወልድ ውሉደ እግዚአብሔር በመንፈስ ቅዱስ መንፈሳውያን የተሰኛችሁ ኦርቶዶክሳውያን አባቶቼ ካህናት ፤ ወንድሞቼ ዲያቆናት ፤ እህቶቼና ወንድሞቼ ሁላችሁም እንደምን ሰነበታችሁልኝ ፡፡

ዕዝራ ሐዲስ(ሊቀ ሊቃውንት) Vs ዕዝራ ሱቱኤል ክፍል አንድ

               

በክርስቶስ ክርስቲያን በወልድ ውሉደ እግዚአብሔር በመንፈስ ቅዱስ መንፈሳውያን የተሰኛችሁ ኦርቶዶክሳውያን አባቶቼ ካህናት ፤ ወንድሞቼ ዲያቆናት ፤ እህቶቼና ወንድሞቼ ሁላችሁም እንደምን ሰነበታችሁልኝ ፡፡ ከሰሞኑ በገባሁት ቃል መሰረት በ2008 ዓ.ም ድርሳነ ቄርሎስን ለሕትመት ያበቁትና በአሁኑ ሰዓት በስሜን ጎንደር ሀገረ ስብከት በመንበረ መንግሥት መድኃኔ ዓለም የዐራቱ ጉባዔያት ትርጓሜ ምስክር መምህር ሊቀ ሊቃውንት ዕዝራ ሐዲስ ቄርሎሱን ሲያሳትሙ ተቀብዓ የሚለውን ተሰብአ እያሉ እየለወጡ፣ በኢሳይያስና በዳዊት ስለ ተቀብዓ የተነገሩ ትንቢቶችን ቆርጠው እያስወጡ የጻፉት መሆኑን ለማሳወቅ እወዳለሁ ፡፡

ዛቲመ ትርጓሜሃ ለቅብዓት እስመ መንፈስ ቅዱስ አንጽሐ ሥጋሁ ለአዳም


በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!
             ክፍል ሦስት
           ======+====
ይድረስ  “frehiwot aregie”
========+==========
1ኛ‹‹‹‹‹‹‹ “3 ንባብ ቅብዓ መንፈስ ቅዱስ ነው ያለው ሲተረጉም የመንፈስ ቅዱስ ቅብአት ተብሎ እንጅ ቅብአት ያለው መንፈስ ቅዱስ አይደለም” ›››››››››››››ብለሃል ፤ ወዳጃችን አክሲማሮስ እየነገረን ያለው “ወአንትሙሰ ቅብዓት ብክሙ እምነ መንፈስ ቅዱስ” እንዳለ ፤ ሕዝቡ አሕዛቡ የጸጋ ልጅነት የተወለድንበት እርሱ መድኅን ክርስቶስ በማኅፀነ እሙ ሰው ስለመሆኑ በሰውነቱ ልደት ባሕርያዊትን ከአብ የተወለደበት ቅብዓቱ መንፈስ ቅዱስ እደሆነ ነው ፡፡ “ይህ ቅብዓት ምንድን ነው ቢሉ መንፈስ ቅዱስ ነው” ብሎ እየነገረን ሳለ ልቡናን እንደፈርዖን ማደንደን አይጠቅምህም  ፡፡

2ኛ‹‹‹‹‹‹‹ “4
ለቅዱሳት መጻሕፍት ረቂቁን ነገር ለመንፈስ ቅዱስ መስጠት ልማድ ነው ።ወልህቀ በመንፈስ ቅዱስ በመንፈስ ቅዱስ አደገ መንመንፈስ ቅዱስ አደረባት እያለ ረቂቁን የመይመረመር ነገር ሁሉ ለመንፈስ ቅዱስ ይሰጣልና ። ስለዚህ ቅብአት ነን ባዮች አስተውሉ”›››››››››››››ብለሃል ወዳጃችን እኛ አንተ ሳትነግረን ቅዱስ መጽሐፍ ረቂቁን ነገር ለመንፈስ ቅዱስ እየሰጠ እንዲናገር በደንብ እናውቀዋለን ፡፡ አስተውል ! መጻሕፍት ረቂቁን ነገር ለመንፈስ ቅዱስ መስጠታቸው እኛ ሰዎች ሥራችንን የምንሰራው በነፍሳችን ሕያዋን ሁነን እንደሆነ ሁሉ ሥላሴም ማንኛውንም ሥራቸውን ሲያከናውኑ በመንፈስ ቅዱስ ሕያው ሁነው ነውና ስለዚህ ነው ፡፡

ትርጓሜሃ ለቅብዓት ክፍል ሁለት


በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!

ዛቲመ ትርጓሜሃ ለቅብዓት እስመ መንፈስ ቅዱስ አንጽሐ ሥጋሁ ለአዳም”  
                              ክፍል ሁለት
==================+====================
ይድረስ  “frehiwot aregie”
========+==========
1ኛ‹‹‹‹‹‹ “3ተኛ ተዋሐደ ተብሎ ይተረጎማል ።ቅብአቶች ከእኛ የሚለዩበት አንዱ ይህ ነው። የፈለገው ቢሆን ቀብአን ተዋሐደ ብለው አይተረጉሙም ግን መጽሐፍ እንዲህ ይላል፦አባ ጊወርጊስ በመጽሐፈ አርጋኖን ላይ እንዲህ ይላል ዘተቀባአከ ስጋሃ ለማርያም ይላል ።ይህ ንባብ የሚተረጎመው የማርያምን ስጋ የተዋሐድህ ተብሎ ነው። ከዚህ ውጭ የፈለገው ሊቂ ይምጣ ሊተረጉመው አይችልም”››››››››ብለሃል ፤ ከዚህ በፊት በክፍል አንድ እንደጻፍኩልህ ከቄርሎስና ከአፈወርቅ ትምህርት ጋር የማይገጥም ነውና በምንም ተዓምር ተቀብዐ ተዋሐደ ተብሎ አይተረጎምም ፡፡ የጠቀስካት የአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ የአርጋኖን መልእክት” ዘተቀባዕከ ሥጋሃ ለማርያም” የሚለው ቃል ትርጓሜው ሰም ለበስ ግስ ነውና ሰም ለበስ ትርጓሜ ይተረጎማል ፡፡ ይህም ማለት  አባ ጊዮርጊስ በአንቀጸ ተቀብዓ ተገብቶ ምሥጢር ስቦታልና ዘተቀባዕከ ሥጋሃ አለው ፤ ትርጓሜው ግን እዚያው አርጋኖን ላይ ቁልጭ ብሎ አለ ይህንን ከተናረ በኋላ “እስመ ክርስቶስ ብሂል ቅቡዕ በከመ ተርጎመ ቄርሎስ ሊቀ ጳጳሳት)” በማለት አስቀምጦታል ፡፡ ቅዱስ ቄርሎስ የተረጎመው ደግሞ “በእንተ ቅብዓት ተሰምየ ክርስቶስ እስመ ክርስቶስ ብሂል ቅቡዕ በመንፈስ ቅዱስ ብሂል” ብሎ ነው ፡፡በመሆኑም ይህች ዘተቀባዕከ ሥጋሃ ለማርያም የሚለው ቃል በሥጋ ማርያም የተቀባህ አንተነህ ማለቱ ነው ይህ የወርቅ አነጋገር ነው ፡፡

“ከዚህ የበለጠ ምሥጢር ምን ምሥጢር አለ?” ክፍል አንድ



በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ!!!

“ከዚህ የበለጠ ምሥጢር ምን ምሥጢር አለ?”

“ለመኑ እመላእክቲሁ ይቤሎ እምአመ ኮነ ወልድየ አንተ ወአነ ዮም ወለድኩከ ፤ ወካዕበ አነ እከውኖ አባሁ ወውእቱ ይከውነኒ ወልድየ (ከሆነ ጀምሮ ከመላእክት ወገን “አንተ ልጄ ነህ እኔ ዛሬ ወለድኩህ፤ ዳግመኛም እኔ አባት እሆነዋለሁ እሱም ልጄ ይሆነኛል” ማንን አለው? ዕብ ምዕ 1 ቁ 5፡፡
==============+==============
በክርስቶስ ክርስቲያን በወልድ ውሉደ እግዚአብሔር የተሰኛችሁ በሜሮን ቅብዓት የታተማችሁ ኦርቶዶክሳውያን ወንድም እህቶቼ እንደምን ሰነበታችሁልኝ! ፡፡ አምላክ በቸርነቱ ጠብቆ ለዚህ ስላደረሰን ክብርና ምሥጋና በፈጠረው ፍጥረት አንደበት ሁሉ ይድረሰው ፡፡ ለዛሬ የምንነጋገርበት ዋና ዓላማችን በዚህ በምሥራቃዊት ምድር ተወልደን አድገን ለከፍተኛ ዘመናዊ ትምህርት ወደ ዘመናዊ መካነ አእምሮ ቀያችንን ለቀን ስንጓዝ በክርስትና ሃይማኖታችን ከተለያዩ አካላት የሚቀርቡ ጥያቄዎች ልቡናችንን እያወኩ ፤ ወደ ሁለተኛ ጥምቀት እያመሩን ስለሆነ መጽሐፍ ቅዱስ ስለምናምናት ክርስትናችን ምን ይላል የሚለውን እውነታ ለማስረዳት ያህል ነው ፡፡

ትርጓሜሃ ለቅብዓት ክፍል አንድ


በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!

ዛቲመ ትርጓሜሃ ለቅብዓት እስመ መንፈስ ቅዱስ አንጽሐ ሥጋሁ ለአዳም”
ክፍል አንድ
===========================+=================================
ይድረስ ለ “frehiwot aregie”
========+==========
መምሕር እንደሆንክ በጽሁፍህ መጨረሻ ላይ ባስቀመጥከው መልኩ ልከህልናል ፡፡ መነሻ ሀሳብህም “ቅብአተ ማለት ምን ማለት ነው?” በሚል ጥያቄ ላይ ተመርኩዘህ ብዙ ነገር ዘላብደሃል ቀባጥረሃልም ፡፡ ቅብዓት ማለት ምን ማለት እንደሆነ በእኔ ገጽ ቅብዓት ማለት ምን ማለት ነው በሚል ርእስ ጽፌልሃለሁና ያንን ገብተህ ተመልከትልኝ እያልኩ በዚህ ዓምድ ስር ወዳጅህ “Hailemariam Mengstie” የተባለ ግለሰብ አሰባስቦ በአንድ ላይ ለለቀቀው ፈጠራችሁ መልስን መስጠት እጀምራለሁ ፡፡ የምጀምረውም “ዛቲመ ትርጓሜሃ ለቅብዓት እስመ መንፈስ ቅዱስ አንጽሐ ሥጋሁ ለአዳም” በሚለው የማቴዎስ ወንጌል አንድምታ ይሆናል፡፡

ቅብዓት ማለት ምን ማለት ነው? ክፍል አንድ


በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ!

ቅብዓት ማለት ምን ማለት ነው? 
==========+==========
ውድ መሢሐውያን (በተለምዶ በአለአዋቂቀው አነጋገር ቅብዓቶች የሚሏችሁ) እናት አባቶቼ ፤ ወንድም እህቶቼ እንደምን አላችሁልኝ ! በዚህ ጽሁፍ ቅብዓት ማለት ምን ማለት እንደሆነ በሰፊው ከቅዱስ መጽሐፍ ማስረጃ እየጠቀስን እያጣቀስን እንነጋገራለን ፡፡ በኦርቶዶክሳዊት ቅድስት ቤተክርሥቲያን ውስጥ ቅብዓት እና ተዋሕዶ ከሦስቱ አካላት አንዱ አካል በተለየ ከዊኑ ቃል በመባል የሚታወቀው ፣ በተለየ ግብሩ ተወላዲ የሆነ አምላክ ወልደ አምላክ ኢየሱስ ክርስቶስ ሰው በመሆኑ የፈጸማቸው ዓበይት ምሥጢራት ናቸው ፡፡ 

እነዚህንም ደጋግ አባቶቻችን አስተምረውናል ፡፡ እንደምን አስተምረውናል ቢሉ ቅዱስ አውሳብዮስ በድርሳኑ መንክረ ገብረ ወልደ እግዚአብሔር ስተ ከርሠ እሙ (የእግዚአብሔር ልጅ በእናቱ ማኅጸን ድንቅ ሥራን ሠራ) ፤ እስመ ፈጸመ ሥርዓተ ተዋሕዶ ወቅብዓት ምዕረ ከመ ቅጽበተ ዓይን (የቅብዓትና የተዋሕዶን ምሥጢር (ሥርዓት) እንደ ዓይን ጥቅሻ አንድ ጊዜ ፈጽሞአልና)” በማለት ይገልጣል ፡፡ ሌሎቹ የሐዲስ ኪዳ መምሕራን ደግሞ በማቴዎስ ወንጌል አንድምታ ምዕራፍ 1 ቁ 16 ላይ ሲዋሐድም ሲቀባም አንድ ጊዜ ነው ከመ ቅጽበተ ዓይን እለሰ የአምኑ ርቱዓ ይሜህሩ ከመ ተቀብዓ ቃል በሥጋሁ ፤ ወእምአመ ኮነ ቃል ሥጋ አሜሃ አስተርአየ በመንፈስ ቅዱስ” ብለው አስተምረውናል ፡፡ ዮሐንስ አፈወርቅም “ወእመ አኮ ቀዲሙ ዘወረደ ወእምዝ ተሠይመ (ቀድሞ ሰው እንዳልሆነ ኋላ እንዳልተሾመ መጠን አንድ ጊዜ ሰው ለመሆን እንደመጣ አስረዳ ፡፡ አንድም ቀድሞ ሰው እንዳልሆነ ኋላ እንዳልተሾመ አስረዳ ፡፡ ሰው ሁኖ ኑሮ ኑሮ ተቀባ የሚሉ አሉና እንዲህ አለ ፡፡ አንድም በተዋሐደ ጊዜ ተቀባ አለ)” (ድርሳን 15 105) ብሏል ፡፡ እንግዲህ በደንብ አስተውል ቅብዓትና ተዋሕዶ አንድ ጊዜ የተፈጸሙ ምሥጢራት መሆናቸውን እንረዳለን ፡፡

የካራ ልጅ በአፍ የጦጣ ልጅ በዛፍ

ሃይማኖት መሢሐዊት!

የካራ ልጅ በአፍ የጦጣ ልጅ በዛፍ የቅብዓት ልጅ በመጽሐፍ!

=================+=================
ወዳጃችን እኛ እኮ ትግላችን እንዲሁ አይደለም ፡፡ የካራ ልጅ በአፍ የቅብዓት ልጅ በመጽሐፍ ስንልም እኮ በአሉ ይባላል በተረት ተረት አይደለም ከዚህ በታች እንደምንመለከተው ባለ ዓይነት ሽንጣም መጽሐፍ ነው እንጅ ፡፡ ሲያምኑ ግማሽ ሲተረጉሙ ዳሽ ማለታችንም እኮ ወደን አይደለም እንዲህ ከዚህ በታች እንደምትመለከቱት ግእዙ ከአማርኛው የማይስማማ የተደናበረ ትርጓሜን እየተረጎሙ ጠፍተው የሚያጠፉ የክፉ ልጆችን ግብር በማስረጃ እያቀረብን እንጅ ፡፡ መተርጉማን የሚሏቸው ከንቱ ሰዎች እንዲህ እያወላገዱ ሲተረጉሙት ስንመለከት ሲተረጉሙ ዳሽ አልናቸው ፤ መድኅን ክርስቶስ በመቀባቱ ክርስቶስ የተባለበትን ምሥጢር ትተው አማኑኤል የተባለባትን (ይህችንም ቢሆን ለሊሁ ቀባዒ ወተቀባዒ ወለሊሁ ቅብዕ ብለው ሲደናበሩ ቢያጠፏትም) ብቻ አንጠልጥለው ሲጓዙ ስናያቸው እና አማኑኤል አምላካችን በሰውነቱ የፈጸማቸውን ድንቅ ድንቅ ነገሮችን ለእነሱ የተመቻቸውን ብቻ እየመራረጡ ሲናገሩ ስንሰማቸው ሲያምኑ ግማሽ አልናቸው ፡፡ 

ታዲያ እንደ አባቶቻቸውና እንደ አያቶቻቸው እንደ አይሁድና ጸሐፍት ፈሪሳውያን ልቡናቸው የደነዘዘ በመሆኑ አሁንም ቢሆን የተሳሳቱ አልመሰላቸውም ፤ መጽሐፉ ግን “በእንተ ቅብዓት ተሰምየ ክርስቶስ” ሲተረጎም ስለ ቅብዓት ክርስቶስ ተባለ ፡፡ “እስመ ክርስቶስ ብሂል ቅቡዕ በመንፈስ ቅዱስ” ክርስቶስ ማለት በመንፈስ ቅዱስ የተቀባ የከበረ ማለት ነውና ይለናል ፡፡