የተቀብዐ ጾመኞችና ሩጫቸው

                        ክፍል ሦስት 

“ዘተወልደ በዳኃሪ መዋዕል በሥጋ ፤ ወተቀብዓ ውስተ ዝንቱ ዓለም በዘይትፌኖ እምኀበ እግዚአብሔር አብ ወተሰምየ ክርስቶስ ፡፡ አኮ በእንተ ካልዕ አላ በእንተ ዘተቀብዓ ፤ እስመ ክርስቶስ ብሂል ቅቡዕ ብሂል ፡፡”

==========================================
አማርኛ ትርጉም
“በኋላ ዘመን በሥጋ የተወለደ ፤ ከእግዚአብሔር አብ በሚገኝ ክብር በዚህ ዓለም የከበረው ፤ ክርስቶስ የተባለው እርሱ ነው ፡፡ በሌላም አይደለም ስለተቀባ ነው እንጅ ፤ ክርስቶስ ማለት የተቀባ ማለት ነውና”
================================
የሊቀ ሊቃውንት ዕዝራ ሐዲስ ትርጉም
“ዘተወልደ በደኃሪ መዋዕል በሥጋ ፤ ወከብረ በዝንቱ ዓለም በዘይትፌኔ እምኀበ እግዚአብሔር አብ፤ ወተሰምየ ክርስቶስ ፤ አኮ በእን ካልዕ ፤ አላ በእንተ በዘተሰብአ ፤ እስመ ክርስቶስ ብሂል አሐዱ እምክልኤቱ ብሂል፤
የአማርኛ ትርጉማቸው፡
“በኋላ ዘመን በሥጋ የተወለደ ፤ ከአብ በሚገኝ ክብር በዚህ ዓለም የከበረው እሱ ነው ፡፡ ከአብ የተገኘም ክብር አካለ ቃል ነው ፡፡ ክርስቶስ ተባለ ፤ በኅድረት አይደለም ፤ ቢዋሐድ ነው እንጅ ፤ ክርስቶስ ማለት በተዋሕዶ ከበረ ማለት ነውና” ብለውታል ፡፡
==============================

የተቀብዐ ጾመኞችና ሩጫቸው (ክፍል አንድ)

ቄርሎስ ስለ ክርስቶስ ተቀባዒነት ከተናገረው

=====+====+===
“እመ ይሬስዮሙ ለመላእክቲሁ መንፈሰ (መላእክትን በዓይን የማይታዩ በእጅ የማይዳሰሱ ረቂቃን አድርጎ የፈጠራቸው ከሆነ ፤ አንድም የፈጠራቸው ሲሆን) ፤ ወመንበር ቦቱ ዘመለኮት (የአምላክነት ሥልጣን ገንዘቡ ከሆነ ፤ አንድም ገንዘቡ ሲሆን) ፤ በእንተ ምንት ተቀብዐ ቅብዓ ትፍሥሕት (እንደምን የደሥታ ዘይትን ተቀባ/ከበረ ብትል) ፤ ወይፈጥር መላእክተ ከመ አምላክ ውእቱ (የባሕርይ አምላክ ነውና መላእክትን ፈጠረ) ፤ ወተቀብዓ ከመ ሰብእ (ሰው በመሆኑ ተቀባ ከበረ) ፤ አኮ በህላዌ መለኮት (በባሕርየ መለኮቱ አይደለም) ፤ አላ ተሰጊዎ ነሥአ ቅብዓተ በሥምረቱ አምላክ ወሰብእ ክርስቶስ (በፈቃዱ ሰው በሆነ ጊዜ ተቀባ ከበረ ተባለ እንጅ ፤ ክርስቶስ አምላክ ነው ሰውም ነው እልሃለው)”
ብራና ምቅዋም 20 ላይ ይገኛል ፡፡ ምቅዋም ማለት ምዕራፍ እንደማለት ነው ፡፡

ጽንዓ ተዋሕዶ ወይስ ጽንዓ ምንታዌ

ክፍል አንድ

ሰሞኑን በሳምባ ምች ምክንያት ጋደም ብየ አንድ መጽሐፍ እያነበብኩ እገኛለሁ ፡፡ የመጽሐፉ ርዕስ ጽንዓ ተዋሕዶ ይባላል ፡፡ በአማን ነጸረ በሚባል ጸሐፊ ሰኔ 2012 . የታተመ መጽሐፍ እንደሆነ ከመግቢያው ይናገራል ፡፡

የመጽሐፉ ርዕስ መሢሐውያን አበው ከጻፉት ወልደ አብ ከተባለው ጉምቱ መጽሐፍ የተወሰደ ስም ነው -ጽንዓ ተዋሕዶ ፡፡ ሀሳቡ ተቀብዐ ተኮር ሐተታዎችንና ታሪኮችን ያነሳሳል ፡፡ ስሙ ደስ ብሎኝ ነበር ነገር ግን ያው እንደሌሎቹ ተዋሕዶዎች እነልዮንን እነ ንስጥሮስን በቃል እየነቀፈ በግብር እነሱን የደገፈ መጽሐፍ ሆኖ አግኝቸዋለሁ ፡፡