“ሲያምኑ ግማሽ ሲተረጉሙ ዳሽ” ክፍል ሦስት
“ሲያምኑ ግማሽ ሲተረጉሙ ዳሽ” ክፍል ሁለት፡፡
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ
“ሲያምኑ ግማሽ ሲተረጉሙ ዳሽ” ክፍል ሁለት
ይድረስ “Habtamu St”››››››ለሚሉህ ግለሰብ
በአስተያየት መስጫ ሳጥን ላይ ለጻፍክልኝ ጥያቄ መልስ
“መናገር ስለምንችል ብቻ ባንናገር መልካም ነው፤እኛ ተበላሽተን ሰውም እያበላሸን ነው”›››››››ብለሃል አዎ ወንድሜ ተበላሽታችሁ ትውልዱን አታበላሹት ነው የእኔም መልእክቴ
1ኛ‹‹‹‹ “በቅባት ነገሰ ማለት እየሱስን የባህሪ አምላክ ያሰኘዋል?”›››››› ”ዘአንገሦ ለሥጋ አዳም በመንፈስ ቅዱስ ወረሰዮ ቅዱሰ ወማኅየዌ--የአዳምን ባሕርይ በመንፈስ ቅዱስ ሕይወትነት ያከበረው የባሕርይ አምላክም ያደረገው እሱ ነው” ሃ.አበው ዘእልሥጦ አግአያ 2፡5
2ኛ‹‹‹‹‹‹‹‹ “.የባህሪ አምላክነትን እያነሳህ ሁለተኛ ከአብ ተቀበለ ማለት ፍጡርነትን አያሳይም?ሶስት ልደት አለዴ?አብ ሁለቴ ወለደው?ስላሴ ዘጠኝ ይሆናል እዴ?”›››››››››››ወንድሜ የባሕርይ አምክ መሆኑን የምታን ከሆነ ያ የባሕርይ አምላክ ሰው ሁኖ የሰውነትን ገንዘብ(መቀበልን) በተዋሕዶ ገንዘቡ በማድረጉ በሰውነቱ ተቀበለ “ወበከመ ለአብ ቦቱ ሕይወት ኀቤሁ ከማ ለወልድኒ ወሀቦ ሕይከወት ከመ ይኩን ሕይወት ኀቤሁ--ለአብ በራሱ ሕይወት እዳው እንዲሁ ለወልድም ሕይወት ይኖረው ዘንድ ሕይወት ዘጠው….እስመ ወልደ እግዚአብሔር ኮነ ወልደ እጓለእመሕያው” ዮሐ 5፡ 26-27 ብሎ ተናገረለት፡፡