ዘመንና ትርጉም (መዝ 44፥7)


"በመካከላችሁ ደግሞ ሐሰተኞች አስተማሪዎች ይሆናሉ፤ እነርሱም የዋጃቸውን ጌታ እንኳ ክደው የሚፈጥንን ጥፋት በራሳቸው ላይ እየሳቡ የሚያጠፋ ኑፋቄን አሾልከው ያገባሉ" ፪ኛ ጴጥ ፪-፩ ብሎ ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ እንደተናገረው የዘመኑ ሊቃውንትና የቀድሞ ሊቃውንት ትርጓሜ ልዩነት እንደልቤ በተባለው የእስራኤል ንጉስ ቅዱስ ዳዊት “በእንተዝ ቀብዐከ እግዚአብሔር አምላክከ ቅብዓ ትፍሥሕት እምእለ ከማከ -- ስለዚህ እግዚአብሔር አምላክህ እንዳንተ ካሉት ይልቅ የደስታ ዘይትን ቀባህ” መዝ 44፥7....... ብሎ የተናገረው እኮ እግዚአብሔር ወልድ በኋለኛው ዘመን ሥጋ አዳምን ሲለብስ የአብ፣ የወልድ፣ የመንፈስ ቅዱስን ግብር በግልጽ መናገሩ እንጅ የሦስቱንም ግብር ጠቅልሎ ለወልድ[ቃል] ብቻ መስጠቱ አይደለምና ልብ ልንል ይገባናል::
......በተዋሕዶ ከበረ ባዮች[ካሮች] “ቀብዓከ እግዚአብሔር አምላክከ -- እግዚአብሔርነትህ አምላክነትህ አከበረህ” ብለው እራሱ አክባሪና ክብር ሥጋ ደግሞ ከባሪ ነው ለሚለው ምንፍቅናቸው መሸፈኛ ይሆን ዘንድ ትርጓሜን እያጣመሙ ይገኛሉ::

ከወልድያ የመጣችው የካሮቹ ጥያቄ


የተከበራችሁ ፡ ኦርቶዶክሳውያን ፡ ሁላችሁም ፡ በማስተዋል ፡ ተከታተሉኝ ፤ ይህች ፡ የካሮቹ ፡ የጨዋ ፡ ጥያቄአቸው ፡ ምንጫ ፡ የምዕራባዊት ፡ ጎጃም ፡ የሊቃውንት ፡ ጉባዔ ፡ ሰብሳቢና ፡ የዐራቱ ፡ ጉባዔ ፡ መምህር ፡ የሚባሉት ፡ የስምዐኮነ ፡ መልአክ ፡ ቃለ ፡ ጽድቁ ፡ ለአብ ፡ የተሰኘች ፡ መጽሐፍ ፡ ናት ፡፡ እኒህ ፡ ሳያላምጡ ፡ የሚውጡ ፡ አግበስብሶች ፡ መጽሐፏን ፡ ሳይመረምሩ ፡ እንዳለች ፡ውጠው ፡ እያነቀች ፡ ገደል ፡ እየለቀቀቻቸው ፡ ይገኛሉ ፡፡ እነሆም ፡ ይሕች ፡ ክሕደት ፡ ከምዕራብ ፡ ጎጃም ፡ ተነስታ ፡ ስሜን ፡ ወሎ ፡ ወልድያ ፡ ደርሳ ፡ ነጥራ ፡ ወደሸዋ ፡ ተመልሳለችና ፡ ክሕደቷን ፡ እንዳለች ፡ አስቀምጥ ፡ እና ፡ በብልት ፡ በብልቷ ፡ ክሽን ፡ ባለች ፡ የኦርቶዶክሳውያን ፡ ልሳን ፡ ለማበጠር ፡ አሐዱ ፡ ብያለሁ፡፡ ሙሉ ፡ ጥያቄው ፡ በቴሌ ፡ ግራም ፡ የደረሰኝ ፡ ሲሆን ፡ እንደሚከተለው ፡ እንደወረደ ፡ አቀርበዋለሁ፡፡ ሰውየው ፡ ሲልክልኝ ፡ “ህይወት” ፡ ያለውን ፡ “ሕይወት” ፡ “ህድረት” ፡ ያለውን ፡ “ኅድረት” ፡ ከማለት ፡ በስተቀር ፡ አልጨመርኩም ፡ አልቀነስኩም ፡፡

ወልደ አብ ክፍል አራት

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሜን!

ወልደ ፡ አብ ፡ በወልደ ፡ አብ ፡ ክፍል ፡ ዐራት

በቅብዓት ፡ የባሕርይ ፡ ልጅ ፡ ሆነ ፡ማለት ፡ ምን ፡ ማለት ፡ ነው?
=============================
በቅብዓት ፡ የባሕርይ ፡ ልጅ ፡ ሆነ ፡ ማለት ፡ ምሥጢሩ ፡ ምንድን ፡ ነው? ፡ ቢሉ ፤ ወልድ ፡ በሰውነቱ ፡ የባሕርይ ፡ ሕይወቱን ፡ መንፈስ ፡ ቅዱስን ፡ በመላ(ካለ ልክ ) ፡ ተቀብሎ ፡ ከአብ ፡ የባሕርይ ፡ ልደትን ፡ ተወለደ ፡ ማለት ፡ ነው ፡፡ ምነው ፡ ይህስ ፡ ቢሆን ፡ በአብ ፡ ያልተወለደ ፣ በራሱ ፡ ያልተወለደ ፣ ስለምን ፡ በመንፈስ ፡ ቅዱስ ፡ ተወለደ? ፡ ቢሉ ፤ ይህስ ፡ ወላዲ ፡ በሚመስለው ፡ ሕይወት ፡ ይወልዳል ፡ እንጅ ፡ በማይመስለው ፡ ሕይወት ፡ አይወለድም ፡፡ ለዚህም ፡ ምሣሌ ፡ ያሥረዳል ፤ እንዴት ፡ ያሥረዳል? ፡ ቢሉ ፤ እነሆ ፡ ዛሬ ፡ በደመ ፡ ነፍስ ፡ ሕያዋን ፡ የሆኑ ፡ እንስሳት ፡  ከእንስሳት ፡ ይወለዳ ፤ በነባቢት ፡ ነፍስም ፡ ሕያው ፡ የሆነ ፡ ሰውም ፡ ከሰው ፡ ይወለዳል ፡፡ በደመ ፡ ነፍስ ፡ ሕያው ፡ ያልሆነ ፡ ከእንስሳ ፤ በነባቢት ፡ ነፍስ ፡ ሕያው ፡ ያልሆነ ፡ ከሰው ፡ እንዳይወለድ ፤ እንደዚህም ፡ ሁሉ ፡ መንፈስ ፡ ቅዱስ ፡ ለአብ ፡ ሕይወቱ ፡ ስለሆነ ፡ በመንፈስ ፡ ቅዱስ ፡ ሕያው ፡ ያልሆነ ፡ ከአብ ፡ አይወለድምና ፡ በመንፈስ ፡ ቅዱስ ፡ ሕይወትነት ፡ ከአብ ፡ ተወለደ ፡፡ “ወበከመ ፡ ለአብ ፡ ቦቱ ፡ ሕይወት ፡ ኀቤሁ ፡ ከማሁ ፡ ለወልድኒ ፡ ወሀቦ ፡ ሕይወተ ፡ ከመ ፡ ይኩን ፡ ሕይወት ፡ ኀቤሁ(ለአብ ፡ በራሱ ፡ ሕይወት ፡ እንዳለው ፡ እንዲሁ ፡ ለወልድም ፡ ሕይወት ፡ ይኖረው ፡ ዘንድ ፡ ሕይወትን ፡ ሰጠው ፤ እስመ ፡ ወልደ እግዚአብሔር ፡ ወልደ ፡ እጓለ ፡ እመሕያው ፡ ውእቱ ፡ (የእግዚአብሔር ፡ ልጅ ፡ የሰው ፡ ልጅ ፡ ነውና))” ፡ እንዳለ ፡ ወንጌለ ፡ ዮሐንስ(ምዕ ፡ 5t 26) ፡፡

የሥሉስ ፡ ቅዱስ ፡ ህልውና

በስመ ፡ አብ ፡ ወወልድ ፡ ወመንፈስ ፡ ቅዱስ ፡ 

አሐዱ ፡ አምላክ

የሥሉስ ፡ ቅዱስ ፡ ህልውና
ዛሬ ፡ የምንመለከተው ፡ ሥላሴ ፡ በህልውና(በአነዋወር) ፡ አንዴት ፡ እንደሆኑና ፤ ቤተ ፡ አይሁድ ፡ ካሮች ፡ ሳይረዱት ፡ ሳያውቁት ፡ ብዙ ፡ ክርስቶሳውያንን ፡ ሁለተኛ ፡ እያጠመቅ ፡ አይሁድ ፡ አረሚ ፡ ለሚያደርጉበት ፡ የክሕደት ፡ ቃል ፡ ፍቱን ፡ መድኃኒት ፡ የሚሆን ፡ መልእክትን ፡ ይሆናል ፤ ይህንን ፡ ቃልም ፡ የጻፍኩላችሁ ፡ ቤተ ፡ አይሁድ ፡ ኬልቄዶናውያን ፡ እቤታቸው ፡ ታቅፈውት ፡ ከሚገኘው ፡ አክሲማሮስ ፡ ከተባለ ፡ የብራና ፡ መጽሐፋቸው ፡ ነው ፡፡ =============================================
የሥላሴ ህልውና እንዴት ነው እንደምን ይኖራሉ ቢሉ ፤ እንደ አንድ ሰው ይኖራሉ ፡፡ የ1ሰው ኑሮው እንዴት ነው ቢሉ ፤ በልቡ አስቦ በቃሉ ተናግሮ በእስትንፋሱ ተንፍሶ ደኅና ሁኖ ይኖራል ፡፡ በልቡ ሲያስብ ቃሉና እስትንፋሱ አይለዩም ፤ በቃሉም ሲናገር ልቡናው እስትንፋሱ አይለዩም ፡፡ ሥላሴም እንዲህ ናቸው ፡፡ ሰው ቃሉ እስትንፋሱ ሳይለየው በልቡ አስቦ ደኅና ሁኖ እንዲኖር ወልድና መንፈስ ቅዱስም ለባውያን በአብ ናቸው ፤ በአብ ያስባሉ ፤ ለወልድና ለመንፈስ ቅዱስ ልባቸው አብ ነው ፤

በተዋሕዶ ከበረ በዝክሪ ወጳውሊ መጽሐፍ

በተዋሕዶ ከበረ ባዮች ምንፍቅና በሊቃውንት መጽሐፍ[በዝክሪ ወጳውሊ ዘደብረ ጽሞና መጽሐፍ]



“የዘማርያን ምንፍቅናና የካሮች[በተለምዶ ተዋሕዶ ብለው ራሳቸውን የሚጠሩ] አስተምህሮ በምስራቅ ጎጃም በምትገኘው ደብረ ጽሞና ገዳም ይኖሩ በነበሩትና ካቶሊካውያንን ተከራክረው የቅዱሳን አበውን ትክክለኛዋን አስተምህሮ ያቆዩልን አባ ዝክሪና አባ ጳውሊ ከሚባሉት ሊቃውንት መጽሐፍ ላይ ተቀንጭቦ የተወሰደ”
~~~~~~~~~~~~//~~~~~~~~~~~~~//~~~~~~~~~~~~~~~
“በአለም ሰገድ በመንግስቱ ዘመን በነገሰ በአስራ አምስት ዓመቱ ክርስቶስ ቀባዒና ተቀባዒ ቅብዕ የሚል ስሙ ዘማርያን የተባለ መናፍቅ ዳግመኛ ተነሳ:: ይሄውም ዘማርያን 
ጀርማናዊው ደቀ መዝሙር ነበር ከእርሱም ትርጓሜውን ሰማ እንደ መምህሩም ሆነ ክርስቶስ ቀባዒና ተቀባዒ ቅብዕ ነው እያለ ያስተምር ጀመር፤
.......ምዕመናንም ሰሙት ምዕመማንም ይህን ትምህርትና ይህን ሃይማኖት ማን አስተማረህ አሉት:: 

.......መናፍቁ ዘማርያንም መለሰ ጌታችን በወንጌሉ እኔ በአብ አብ በእኔ እኔና አብ አንድ ነን ያለውን እርሱ ምስክሬ ነው አላቸው:: እኔም ይህን ነገር አውቄ አብ ከወልድ ጋር ካለ ስለዚህ ክርስቶስ ሌላ ቀባዒና ቅብዓትን አይፈልግም እርሱ ቀባዒ እርሱም ተቀባዒ እራሱም ቅብዕ ነው እላለሁ አለ:: 

ወልደ ፡ አብ ፡ በወልደ ፡ አብ : ክፍል ፡ ሦስት

ወልደ ፡ አብ ፡ በወልደ ፡ አብ : ክፍል ፡ ሦስት
==================================
የጌታችን ፡ የባሕርይ ፡ ልጅነት ፡ እና


የቤተ ፡ አይሁድ ፡ ካሮች ፡ ውድቀት
======================================
በባለፈው ፡ መልእክት ፡ ቤተ ፡ አይሁድ ፡ ካሮች ፡ ለእመቤታችን ፡ የምንሰግደው ፡ ስግደት ፡ የወልደ ፡ እግዚአብሔር ፡ የባሕርይ ፡ ልጅነት ፡ ያጠይቃል ፡ በሚለው ፡ ሀሳብ ፡ ዙሪያ ፡ ላይ ፡ በሰፊዉ ፡ ተነነጋግረናል ፡፡ እኒህ ፡ ቤተ ፡ አይሁድ ፡ ካሮች ፡ ነጠላ ፡ ቃል ፡ እየመዘዙ ፡ ራሳቸውን ፡ ከጥልቅ ፡ ጉድጓድ ፡ ሲገቡ ፡ ይስተዋላሉ ፡፡ “ለመስቀል ፡ መሰገዱ ፡ የእሱን ፡ የባሕርይ ፡ ልጅነት ፡ ያጠይቃል ፡ እንዴት ፡ ቢሉ ፤ እንግዲያው ፡ የቅዱስ ፡ ጴጥሮስ ፡ የቅዱስ ፡ ጊዮርጊስ ፡ መስቀል ፡ ይሰገድለታልን ፤ ስንኳንስ ፡ ለመስቀሉ ፡ ለርሳቸው ፡ አይሰገድላቸውም ፤መስቀል ፡ ግን ፡ የባሕርይ ፡ ልጅ ፡ የሆነው ፡ ሥጋው ፡ ቢፈስበት ፤ ደሙ ፡ ቢፈስበት ፡ እሰግድ ፡ ለመስቀለ ፡ እግዚእነ ፡ ኢየሱስ ፡ ክርሰቶስ ፡ ዘተቀደሰ ፡ በደሙ ፡ ክቡር” ፡ ብለን ፡ እንሰግድለታለን›››››››ወልደ ፡ አብ ፡ ገፅ ፡ 251 ፤ ተብሎ ፡ የተቀመጠውን ፡ ቃል ፡ ሙሉውን ፡ ሳይቀበሉና ፡ ሳይመለከቱ ፡ “ስንኳንስ ፡ ለመስቀሉ ፡ ለርሳቸው ፡ አይሰገድላቸውም” ፡ የምትለዋን ፡ ቁንጽል ፡ ሀሳብ ፡ እያነሱ ፡ ለመስቀል ፡ አይሰገድም ፡ ለጻድቃንም ፡ አይሰገድም ፡ ብላችኋል ፡ እያሉ ፡ የጅል ፡ ንግግር ፡ ይናገራሉ ፤ ራሳቸው ፡ ቈናጽላን ፡ መሆናቸውን ፡ እንኳን ፡ አልተረዱም ፡፡ እነሱ ፡ እድሜ ፡ ልካቸውን ፡ እንደዚህ ፡ ይላሉ ፣ አከሌ ፡ ተሐድሶ ፡ ነው ፣ እሌ ፡ መናፍቅ ፡ ነው …..ሌላም ፡ ሌላም ፡ እያሉ ፡ የሰው ፡ ስም ፡ መስበር ፡ እንጅ ፡ የእነሱ ፡ ክሕደትና ፡ ውድቀት ፡ አይታያቸውም ፡፡ ሲያሻቸው ፡ ቅብዐት ፡ የሚለውን ፡ ተዋሕዶ ፡ እያሉ ፡ በነሲብ ፡ በመተርጐም ፣ ሲያሻቸው ፡ ተቀብዐ ፡ የሚሉ ፡ ቃላትን ፡ ከቅዱስ ፡ መጽሐፍ ፡ እየቆረጡ ፡ በማውጣት ፣ ሲያሻቸው ፡ ደግሞ ፡ የዋሁን ፡ ምእመን ፡ እንዲህ ፡ ቁንጽልጥል ፡ እያደረጉ ፡ እያወጡ ፣ ሲያሻቸው ፡ ደግሞ ምንጭ ፡ የሌለው ፡ አሉባልታና ተረት ፡ ተረት ፡ አንዲት ፡ ጥቀትን ፡ ሁለተኛ ፡ እያጠመቅ ፡ እያደሱ ፡ ሌላውን ፡ ተሐድሶ ፡ እያሉ ፡ ይሳደባሉ ፤ ክርስቲያኖችንም ፡ እስላ ፡ አረሚ ፡ አይሁድ ፡ ከሐዲ ፡ ያደርጋሉ ፡፡ ልቡና ፡ ያላችሁ ፡ ሁላሁም ፡ እኔ ፡ ዘወትር ፡ የሚያንገበግበኝና ፡ ሥራየን ፡ ሁሉ ፡ ትቼ ፡ የምጽፍላችሁ ፡ ሥልጣን ፡ አስፈልጎኝ ፤ አልያም ፡ የምሠራው ፡ ሥራ ፡ ስለሌለኝ ፡ ተረ ፡ ረብ ፡ ጥቅም ፡ ማግኘት ፡ ፈልጌ ፡ ሳይሆን ፤ እውነትን ፡ እያየሁ ፡ ብዙዎች ፡ ሲቀብሯት ፡ ዝም ፡ ማለት ፡ ስለሌለብኝ ፡ ነው ፡፡ ለምድዊ ፡ ድሎትና ፡ ምቾት ፡ አምላክ ፡ በቸርነቱ ፡ ለደመወዝ ፡ የምትሆን ፡ ሥራ ፡ ሰጥቶኝ ፡ እኔንም ፡ ቤተሰቤንም ፡ በፈጣሪ ፡ ቸርነት ፡ እያኖርኩባት ፡ ነው ፡፡  

ወልደ ፡ አብ ፡ በወልደ ፡ አብ : ክፍል ፡ ሁለት

ወልደ ፡ አብ ፡ በወልደ ፡ አብ : ክፍል ፡ ሁለት
==================================
የጌታችን ፡ የባሕርይ ፡ ልጅነት ፡ እና


የቤተ ፡ አይሁድ ፡ ካሮች ፡ ውድቀት
======================================
በገዛ ፡ ሥልጣኔ ፡ ተነሣሁ ፡ ሲል ፡ ለወልድ ፡ ከአብ ፡ ከመንፈስ ፡ ቅዱስ ፡ የተለየ ፡ ሥልጣን ፡ አለውና ፡ በተለየ ፡ ሥልጣኔ ፡ ተነሣሁ ፡ ሲል ፡ ነውን? ፡ ቢሉ ፤ ከአብ ፡ ከመንፈስ ፡ ቅዱስ ፡ ጋር ፡ በሥልጣን ፡ ዕሪናውን ፡ ሲያጠይቅ ፡ እጅ ፡ የተነሣስ ፡ በ3ቱም ፡ ሥልጣን ፡ ነው ፡፡ “አማን ፡ በአማን ፡ ተንሥአ ፡ እሙታን ፡ በኃይለ ፡ አቡሁ ፡ ወመንፈስ ፡ ቅዱስ ፡ በሥልጣኑ ፡ ፈቲሆ ፡ ማዕሠሮ ፡ ለሞት()” ፡ እንዳለ ፡ ድርሳነ ፡ ማኅየዊ() ፡፡ በ3ቱም ፡ ሥልጣን ፡ እንደተነሣ ፡ ሊቃውንቱ ፡ በዝርዝር ፡ ተናረዋል ፡፡
በአብ ፡ ሥልጣን ፡ እንደተነሣ ፡ ቅዱስ ፡ ጳውሎስ ፡ “አብ ፡ አንሥኦ ፡ ለወልዱ ፡ እሙታን” ፡ ብሏል ፡፡ በገዛ ፡ ሥልጣኑ ፡ እንደተነሣ ፡ ቅዱስ ፡ ቄርሎስ ፡ “ወተንሣእኩ ፡ በሥልጣነ ፡ ባሕቲትየ” ፡ ብሏል ፡፡ በመንፈስ ፡ ቅዱስ ፡ ሥልጣን ፡ እንደተነሣ ፡ ባስልዮስ ፡ ዘቂሣርያ ፡ “ወተንሥአ ፡ በኃይለ ፡ መለኮቱ”  ፡ ብሏል(ሃይ.አበው ፡ ምዕ ፡ 34 ፡ ክ ፡ 5 t18) ፡፡ ኃይል ፡ የተባለ ፡ መንፈስ ፡ ቅዱስ ፡ እንደሆነ ፡ ለማጠየቅ ፡ ወንጌለ ፡ ሉቃስ(ምዕ ፡ 24t49) ፡ “ወናሁ ፡ እፌኑ ፡ ተስፋሁ ፡ ለአቡየ(እኔም ፡ ተስፋ ፡ መንፈስ ፡ ቅዱስን ፡ እልክላችኋለሁ) ፡ ወአንትሙሰ ፡ ንበሩ ፡ ሀገረ ፡ ኢየሩሳሌም ፡ እስከ ፡ ትለብሱ(እናንተ ፡ ግን ፡ ከሰማይ ፡ ሀይልን ፡ ማለት ፡ ሰማያዊ ፡ ሀብትን ፡ እስክትለብሱ ፡ በኢየሩሳሌም ፡ ኑሩ)” ፡ ብሏል ፡፡ይህስ ፡ ይሁን ፡ በሥልጣነ ፡ ባሕቲትየ ፡ ማለቱ ፡ በብቻየ ፡ ሲል ፡ አይደለምን? ፡ ቢሉ ፤ ይህስ ፡ ትንሣውን ፡ ሲያይ ፡ የተናረው ፡ ነው ፡፡ ማለትም ፡ አብና ፡ መንፈስ ፡ ቅዱስ ፡ እንደሱ ፡ ሰው ፡ አልሆኑም ፤ እሱ ፡ ግን ፡ ሰው ፡ የሆንኩ ፣ ከሙታን ፡ የተነሣሁ ፡ በተለየ ፡ አካሌ ፡ እኔ ፡ ብቻ ፡ ነኝ ፡ ሲል ፡ “ወተንሣእኩ ፡ በሥልጣነ ፡ ባሕቲትየ” ፡ አለ ፡ እንጅ ፡ ከአብና ፡ ከመንፈስ ፡ ቅዱስ ፡ የተለየ ፡ ሥልጣን ፡ አለኝ ፡ ሲል ፡ አይደለም ፡፡
ዳግመኛም ፡  የጸጋ ፡ ልጅ ፡ የግድ ፡ ይታመማል ፣ የግድ ፡ ይሞታል ፡ እንጅ ፡ በፈቃዱ ፡ አይታመምም ፣ በፈቃዱ ፡ አይሞትም ፤ እርሱ ፡ ግን ፡ የባሕርይ ፡ ልጅ ፡ ነውና ፡ በፈቃዱ ፡ ታመመ ፡ ሞተ ፤ “ሞተ ፡ በፈቃዱ ፡ ወተቀብረ ፡ በሥምረቱ” ፡ እንዳለ ፡ ዮሐንስ ፡ ነባቤ ፡ መለኮት ፡፡ ዳግመኛም ፡ የጸጋ ፡ ልጅ ፡ የራሱን ፡ ይታመማል ፡ ይመሞታል ፤ “እመሰ ፡ ኀደረ ፡ ቃል ፡ ላዕሌሁ ፡ ከመ ፡ ኵሎሙ ፡ ነቢያት ፡ ለምንትኑ ፡ ኢተብህለ ፡ በእንተ ፡ ግብሮሙ ፡ እምልደቶሙ ፡ እስከ ፡ ዕለተ ፡ ሞቶሙ ፡ ኮነ ፡ በእንቲአነ ፡ አላ ፡ በእንተ ፡ ርእሶሙ ፡ ባሕቲቶሙ(በነቢያት ፡ ሁሉ ፡ እንዲያድር ፤ ቃል ፡ ከአደረበት ፡ ከተወለዱ ፡ ጀምሮ ፡ እስከ ፡ ሞታቸው ፡ ድረስ ፡ የሠሩት ፡ ሥራ ፡ እኛን ፡ ለማዳን ፡ ተደረገ ፡ ለምን ፡ አልተባለም? ፡ ራሳቸውን ፡ ብቻ ፡ ለማዳን ፡ እንደሆነ ፡ ተነገረ ፡ እንጅ ፡፡  
እመሰ ፡ ኀደረ ፡ ላዕሌሁ ፡ ቃል ፡ ከመ ፡ ኩሎሙ ፡ ነቢያት(በነቢያት ፡ ሁሉ ፡ እንዲያድር ፡ ቃል ፡ ከአደረበት) ፤ ለምንትኑ ፡ ተብህለ ፡ በእንተ ፡ ዝንቱ ፡ ባሕቲቱ ፡ ዘተወልደ ፡ እምእግዝእትነ ፡ ቅድስት ፡ ድንግል ፡ ማርያም ፡ ምዕረ ፡ ቦአ ፡ ውስተ ፡ ዓለም ፡ በደኃሪ ፡ መዋዕል(ከእግዝእትነ ፡ ማርያም ፡ ስተወለደ ፡ ስለእርሱ ፡ ብቻ ፡ 5500 ፡ ዘመን ፡ ሲፈጸም ፡ አንድ ፡ ጊዜ ፡ ሰው ፡ ሁኖ ፡ ተወለደ ፡ ተብሎ ፡ ለምን ፡ ተነገረ)” ፡ እንዳለ ፡ አትናቴዎስ(ሃይ.አበው ፡ ምዕ ፡ 31t31-32) ፡፡ ጌታ ፡ ግን ፡ የባሕርይ ፡ ልጅ ፡ የባሕርይ ፡ አምላክ ፡ ነውና ፡ ለሰው ፡ ብሎ ፡ ታመመ ፡ ሞተ ፤ “ሞተ ፡ ከመ ፡ ያሕይዎሙ ፡ ለምውታን” ፡ እንዳለ ፡ ዮሐንስ ፡ ነባቤ ፡ መለኮት ፡፡
ምነዋ ፡ የጸጋ ፡ ልጆች ፡ ጻድቃን ፣ ሰማዕታት ፡ መታመማቸው ፣ መሞታቸው ፡ በፈቃዳቸው ፡ አይደለምን?፡ እንደምን ፡ የግድ ፡ ይሆናል? ፡ ቢሉ ፡ ጌታ ፡ ሲአስተምር ፡ በወንጌለ ፡ ማቴዎስ(ምዕ ፡ 1t36) ፡ ላይ ፡ “ዘኢሐደገ ፡ አባሁ ፡ ወእሞ ፣ ቤቶ ፡ ወዉሉዶ ፡ ወዘኢፆረ ፡ መስቀለ ፡ ሞትየ ፡ ኢይክል ፡ ይፀመደኒ” ፡ ብሎ ፡ እንደገለጸው ፤ እናት ፡ አባቱን ፣ ቤት ፡ ንብረቱን ፡ ትቶ ፡ እኔን ፡ ያልተከተለ ፡ ከእኔ ፡ አንድነት ፡ የለውም ፡ መንግሥተ ፡ ሰማያትን ፡ እንኳንስ ፡ ሊገባባት ፡ አያያትም ፡ ብሎ ፡ አዋጅ ፡ ተናግሯል ፡፡ ጻድቃን ‹ ሰማዕታትም ፡ ይህ ፡ አዋጅ ፡ ግድ ፡ ብሏቸው ፡ ይታመማሉ ፡ ይሞታሉ ፡ እንጅ ፡ በፈቃዳቸው ፡ አይታመሙም ፡ አይሞቱም ፤ እሱ ፡ ግን ፡ ይጸድቅበታል ፡ እንዳይባል ፡ በባሕርዩ ፡ ጻድቅ ፤ ይብርበታል ፡ እንዳይባል ፡ የባሕርይ ፡ ክቡር ፡ ነውና ፡ ለሰው ፡ ሲል ፡ በፈቃዱ ፡ ታመመ ፡ ሞተ ፡:

ወልደ ፡ አብ ፡ በወልደ ፡ አብ ክፍል ፡ አንድ


የጌታችን ፡ የባሕርይ ፡ ልጅነት ፡ እና ፡


የቤተ ፡ አይሁድ ፡ ካሮች ፡ ውድቀት
======================================
ወንድሞች ፡ እህቶች ፡ እንደምን ፡ አላችሁልኝ?ሕይወት ፡ እንዴት ፡ ነው?ሁሉም  ሠላም?አምላክ ፡ ይመሥገን ፡፡ የዛሬው ፡ መልእክቴ ፡ የሚያተኩረው ፡ በቅርቡ ፡ አንዳንድ ፡ ወንድሞች ፡ “እናንተ ፡ ቅብዐቶች ፡ ለመስቀልና ፡ ለጻድቃን ፡ ስግደት ፡ አይገባም ፡ ብላችሁ ፡ ጽፋችኋል ፡ በመጽሐፋችሁ” ፡ እያሉ ፡ ሲከሱን ፡ ሲወቅሱን ፡ አስተውያለሁ ፡፡ የቅብዐቱን ፡ ጣዕመ ፡ ምሥጢር ፡ ሳያውቁት ፡ በልካችን ፡ እያበዙ ፡ አንድ ፡ መንፈስ ፡ ቅዱስን ፡ ሲበዘብዙት ፡ ብንመለከትም ፡ የፍርዱ ፡ ባለቤት ፡ አምላክ ፡ እሱ ፍርዱን ፡ ያስቀምጣል ፡ ፡ ማቴ 12፡ 32 ፤ ብዙ ፡ ወንድሞችና ፡ እህቶችንም ፡ በዚህ ፡ ቃል ፡ ምክንያት ፡ ድጋሚ ፡ አጥምቀው ፡ እስላም ፡ አረሚ ፡ አድርገውበታል ፤ እያደረጉበትም ፡ ይገኛል ፡፡ ስለዚህ ፡ እውነታው ፡ ምን ፡ እንደሆነ ፡ መጻፍ ፡ ስላለብኝ ፡ ከመጽሐፉ ፡ ያለውን ፡ ቃል ፡ ሳልጨምር ፡ ሳልቀንስ ፡ እንዲህ ፡ አርበዋሁ፡፡ አንብብዋ ፡ ለመልእት ፡ እምጥታ ፡ እስከ ተፍጻሜታ ፤ እንዲሉ ፤ ከመጀመሪያው ፡ እስከመጨረሻው ፡ ሳያነቡ ፡ የወደቁት ፡ ካሮች ፡ እኛን ፡ ማላመጥ ፡ አፋቸውን ፡ መፍቻ ፡ ስላደረጉት ፡ ነው ፡ እንጅ ፤ በወልደ ፡ አብ ፡ ላይ ፡ የተገለጠው ፡ ቃል ፡ ለቅዱሳንና ፡ ለመስቀል ፡ ስግደት ፡ አያስፈልግም ፡ የሚል ፡ አይደለም ፡፡ ስለሆነም ፡ የመጽሐፉን ፡ ሙሉ ፡ ኃይለ ፡ ቃል ፡ እንደሚከተለው ፡ ላስነብባሁ፡፡

ወልድ በሥጋው ሞተ እንደተባለ በሥጋው ፍጡር እንደሚባል የአበው ምስክር




፩ኛ............  “ወንነጽር  ለለ፩ዱ ቃል እምቃላት ወኃይለ ዘውስቴቶሙ ወንትናገር ዳግመ ምክንያተ ነገር ዘይቤልዎ ዘከመ ትስብእቱ ናሁ ------ ከመጽሐፍት ቃላት እያንዳንዱን ቃላት በውስጣቸውም ያለውን ምስጢር እናስተውል፤ ሰው እንደመሆኑ የተነገሩለትን፤ የነገሩንም ምክንያት ዳግመኛ እንናገር::  ዮሐ 5፥39 ፤
 ናሁ አቅደምነ ወተናገርነ ባህሎ  ዘይቤ አምላኪየ ዘውእቱ አምላክክሙ ብዙኃ ጊዜያተ ከመ ይለቡ ዘአልቦቱ አእምሮ ፍናወ ፩ዱ ቃል ወዘተብህለ ከመ ውእቱ ሰብእ ወአልቦ ዘየአምሮ----  ይኸውም ፈጣሪያችሁ ነው፤ እነሆ አምላኪየ ያለበትን ነገር አስቀድመን መላልሰን ተናግረናልና፤ ሰው  እንደሆነ የሚያውቀውም እንደሌለ የተናገረለትን እያንዳንዱን ቃል መንገድ (ምስጢር) ዕውቀት የሌለው ሰው ያውቅ ዘንድ ፤
  ወበዝንቱ ቃለ መጽሐፍ ቅዱስ ይትዐወቅ ከመ ውእቱ እም፪ቱ ዘያስተርኢ ወዘኢያስተርኢ ፩ዱ ሕላዌ በእንተሰ ዘያስተርኢ ይቤ አምላኬየ ወበእንተ ዘያስተርኢ ይቤ አቡየ ---- በዚህም በቅዱሳት መጽሐፍት ቃል እርሱ ከሚታየውና ከማይታየው ከሁለቱ አንድ አካል አንድ ባሕርይ እንደሆነ ይታወቃል፤ ስለ ክበበ ትስብእት አምላኪየ አለ ስለ መለኮት አባቴ አለ::
ወአልቦ ዘይክል መኑሂ ያውሥእ ቃለ በእንተ እሉ ፪ቱ ሥርዓታት እፎኑ ውእቱ ሰብእ ዘኢኮነ ፍጡረ  ወለእመ ኢኮነ ሰብአ እፎመ ተሰምየ ሰብአ ---- አባቴ አምላኪየ ስለ አላቸው ስለ እነዚህ ምስጢራት መልስ ሊሰጥ የሚችል የለም፤ ፍጡር ያይደለ ሰው እንደምን ያለ ነው? ሰውስ ካልሆነ እንዴት ሰው ይባላል? ” ሃይ/አበው  ዘኤጲፋንዮስ ምዕ 54፥16 – 19 ይላል::
፪ኛ........... “ወዘሰ ንቤ ፍጡር ውእቱ በእንተ ዘተሣተፈ ሥጋ ድካምነ በሥርዓት ዘገብሮ በእንቲአነ-- ፍጡር[ሰው] ነው ያልነውም ስለ እኛ ባደረገው ተዋሕዶ ደካማ ባሕርያችንን ስለተዋሐደ ነው” ሃይ/ አበው ዘጎርጎርዮስ 35፥3

በእውኑ ቅዱስ ቄርሎስ ቅብዓትን አውግዟልን?

በተለምዶ ተዋሕዶዎች ተብለው የሚጠሩ ትክክለኛ ስማቸው ግን ካሮች መሲሕ በመንፈሰ አቡሁ ብለን የምናምነውንና መሲሐዊያን፣ ቅብዓን፣ ናዝራዊያን ተብለን የምንጠራውን እኛን ለማጭበርበር ሲፈልጉ ቅብዓትን እኮ ቅዱስ ቄርሎስ አውግዞታል ይሉናል:: እውነታውን ግን አብረን እንየው:- 
ብዙዎቹ በተዋሕዶ ከበረ ብለው የሚያምኑ ሰዎች “ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን በእርሱ አጋዥነት ድንቅ ተአምራትን ያደርግ ዘንድ በመንፈስ ቅዱስ ከበረ የሚለው ፤ ርኩሳን አጋንንትን በማውጣት ጊዜም ኃይልን ተአምራትን ከመንፈስ ቅዱስ ይቀበላል በሰውም የአምላክነትንም ሥራ እርሱ ራሱ ይሠራል የማይል ቢኖር ውጉዝ ይሁን ሃይ/ አበው ዘቄር 73÷49” በማለት አውግዟችኋል ይሉናል::

እውነት አለቀሰች






                                   ልብ ያለህ አስተውል፣ ጆሮ ያለህ ስማ፣
                                  እግርህ እንዳይገባ ከክህደት ከተማ::
                                  የያዝከውን አጽና ልብህ አይጨነቅ፣
                                  ለጥያቄህ መልስም ሊቃውንትን ጠይቅ::
                                  ለእውነት የቆመ ሃይማኖቱን የሚያውቅ፣
                                  ንባብ ትርጓሜን ጠንቅቆ የሚዘልቅ፣
                                  ተናገር ዮሐንስ አንተ ልሳነ ወርቅ::