ባሕረ ሐሳብ ክፍል ሦስት

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ!

መሢሐውያን ወንድም እህቶቼ እናት አባቶቼ እንደምን አላችሁ? 

በዛሬው መልዕክቴ የ2014 ዓ.ም ምህረት ዘመን በዓላትና አጽዋማት የሚውሉባቸውን የባሕረ-ሐሳብ ቀመሮችን ቀለል ባለ አቀራረብ ይዤላችሁ መጥቻለሁ ፡፡
ለመግቢያ ያህል ነቢየ እግዚአብሔር ክቡር ዳዊት ስለዘመን መቀያየርና ዘመንን ሲለሚለውጠው የዘመናት ባለቤት እንዲህ ሲል የተናገረውን ላስነብባችሁ ወደድኩ፡፡

“ሐወጽካ ለምድር ወአርወይካ ( ይህችን ዓለም በረድኤት ጎበኘሃት አንድም ኢየሩሳሌምን ከሰብዓ ዘመን በኋላ በረድኤት ጎበኘሃት ፤ ማለት የዘሩባትን እንድታበቅል የተከሉባትን እንድታጸድቅ አደረግሃት)፤ አንድም ትሩፍን ከሰብዓ ዘመን በኋላ በረድኤት ጎበኘኻት) ፤ አንድም ምእመንን ከአምስት ሽህ አምስት መቶ ዘመን በኋላ በልጅነት ጎበኘሃት።