ባሕረ ሐሳብ ክፍል ሦስት

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ!

መሢሐውያን ወንድም እህቶቼ እናት አባቶቼ እንደምን አላችሁ? 

በዛሬው መልዕክቴ የ2014 ዓ.ም ምህረት ዘመን በዓላትና አጽዋማት የሚውሉባቸውን የባሕረ-ሐሳብ ቀመሮችን ቀለል ባለ አቀራረብ ይዤላችሁ መጥቻለሁ ፡፡
ለመግቢያ ያህል ነቢየ እግዚአብሔር ክቡር ዳዊት ስለዘመን መቀያየርና ዘመንን ሲለሚለውጠው የዘመናት ባለቤት እንዲህ ሲል የተናገረውን ላስነብባችሁ ወደድኩ፡፡

“ሐወጽካ ለምድር ወአርወይካ ( ይህችን ዓለም በረድኤት ጎበኘሃት አንድም ኢየሩሳሌምን ከሰብዓ ዘመን በኋላ በረድኤት ጎበኘሃት ፤ ማለት የዘሩባትን እንድታበቅል የተከሉባትን እንድታጸድቅ አደረግሃት)፤ አንድም ትሩፍን ከሰብዓ ዘመን በኋላ በረድኤት ጎበኘኻት) ፤ አንድም ምእመንን ከአምስት ሽህ አምስት መቶ ዘመን በኋላ በልጅነት ጎበኘሃት።

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክሳዊት ቤተ-ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተላለፈ ቃለ-ግዘት

 

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፡፡

እኛ በኢትዮጵያ(ጎጃም) የምንኖር ኦርቶዶክሳውያን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ-ክርስቲያንን ሕግና ሥርዓት ጠብቀንና አምነን መቆየታችን አሁንም እየጠበቅን የምንገኝ መሆናችን የሚታወስ ነው ፡፡ በዚህ ቆይታ ወደኋላ መለስ ብለን ስለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ-ክርስቲያን ታሪካዊ ክስተት ብንመለከት የውጭ ሀገር ሚሲዮኖች ወደ ሐገራችን በመምጣታቸው በቤተ ክርስቲያኒቱ ላይ ልዩ ችግር ተፈጠረ ፡፡ ሆድ አደር ሊቃውንትም አንዲት የቀናች መንገድን (ኦርቶዶክስን) በውጭ ጠላት ገንዘብና ሹመት ተደልለው፤በምፀት አነጋገርና በጥላቻ መንፈስቅብዐት፣ ካራ፣ ፀጋ ፤ ሚናስ ፤ ፃማበመበባል እርስ በእርሳቸው ይነቃቀፉ እንደነበር የታሪክ መጻሕፍትን አገላብጦ መመልከት ይቻላል ፡፡