ዜና ትንሣኤሁ ለኢየሱስ ክርስቶስ (ክፍል ሁለት )

ከክፍል አንድ በቀጥታ የቀጠለ

ወማርያምሰ ቆመት ኀበ መቃብር አፍአ ወትበኪ
ማርያም ግን ከመቃብር አጠገብ ሁና ታለቅስ ነበር ፡፡
ወእንዘ ትበኪ ሐወጸት ውስተ መቃብር
እያለቀሰች ወደ መቃብር በተመለከተች ጊዜ
ወርእየት ክልኤተ መላእክተ በጸዓድው አልባስ
ሁለት መላእክት ብሩህ ብሩህ (ነጭ ነጭ) ልብስ ለብሰው
ወይነብሩ አሐዱ ትርኣሰ ወአሐዱ ትርጋጸ ኀበ ነበረ ሥጋሁ ለእግዚእ ኢየሱስ
የጌታችን ሥጋ ካለበት ቦታ አንዱ በራስጌ አንዱ በግርጌ ተቀምጠው አየች ፡፡

ዜና ትንሣኤሁ ለኢየሱስ ክርስቶስ (ክፍል አንድ )

እነሆ የክርስቶስን ትንሣኤ የሚያወሱ ዐበይት ቃላትን ከዕለቱ ሥርዓተ ቅዳሴና የዋዜማ ሥርዓት ለአዘክሮት እንመልከት ፡፡
==========================
“የመጀመሪያው (ከቅዳሴ በፊት የሚሰበከው ምስባክ)
==============================
“ወተንሥአ እግዚአብሔር ከመ ዘንቃህ እምንዋም
ወከመ ኃያል ወኅዳገ ወይን
ወቀተለ ጸሮ በድኅሬሁ”
መዝሙር 77 ፡65
አንድምታ ትርጉም
“ወተንሥአ እግዚአብሔር ከመ ዘንቃህ እምንዋም ፤ ወከመ ኃያል ወኅዳገ ወይን ፤ ወቀተለ ጸሮ በድኅሬሁ” ”
የተኛ ሰው ፈጥኖ እንደሚነሳ እግዚአብሔርም ከሰባ ዘመን በኋላ ፈጥኖ በረድኤት ተነሣ
ከመ ዘኃደጎ ሥካረ ወይን ይላል አብነት የወይን ሥካር እንዳለፈለት ሰው አንድም ከመ ኅዱግ ወይን ይላል አበርትቶ እንደተጣላ ወይን ፡፡ በሀገራቸው ፅኑ መጠጥ አለ ሰው የጠጣው እንደሆነ ሦስት ቀን ወድቆ ይሰነብታል ፡፡