በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!
=====+=====+====
ጾመ ነቢያት መቼ ፤ ለምን ( ክፍል አንድ)
====+===+====
ኦርቶዶክሳዊው ጾመ ነቢያት በዐራቱም ዘመናት (በማቴዎስ ፣ በማርቆስ ፣ በሉቃስ ፣ በዮሐንስ) ኅዳር 19 ቀን ይገባል ታኅሣሥ 29 ይፈታል።
------------------------------------------------------------
ልዑለ ባሕርይ ቅዱስ እግዚአብሔር አዳምን በአርያውና በአምሳሉ ፈጥሮ በፈጠረው በ40 ቀኑ በመንፈስ ቅዱስ አክብሮ ገነት አስገባው ፡፡ አዳም ግን በደለ ፤ ከገነትም ተባረረ ፤ በምድረ በዳዋ በደብረ ቅዱስም ተቀመጠ ፤ በጥንተ ጠላቱ ሠይጣንም ሥቃይና መከራን ተቀበለ ፡፡
በዚህም አንጻር በ40 ቀኑ ያጣትን ገነትን ያወርሰው ዘንድ ፤ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ይወርዳል ይወለዳል ፤ አዳምንም ከግዞት ከባርነት ነጻ ያወጣዋል ብለው ነቢያት የጾሙት ጾም ነው ፡፡ ጾሙ 40 መዓልት 40 ሌሊት ነው ፡፡ “ጾመ ሙሴ ዐርብዓ መዓልተ ወዐርብዓ ሌሊተ” እንዳለች ኦሪት ፡፡ ከ40 ቀን በላይ ጾመ ተብሎ የተጻፈለት አንድም ነቢይ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ አይገኝም ፡፡ 40 ቀን የሚሆነው ጾሙን ኅዳር 19 ስንጀምር ነው ፡፡
ነገር ግን “62ኛው የግብጽ ጳጳስ አብርሃም ሶርያዊ ሦስት ቀን በመጾም ተራራ አንቀሳቅሶ ከመናፍቃን ሕዝቡን ያዳነባት ጾም ናትና ከ40ው ጾም ጋር መጨመር አለባት” እያሉ የሚከራከሩ ሰዎች አሉ ፡፡
